የመካነ ሰላም መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ለመጀመሪያ ጊዜ በአቡነ መልከጼዴቅ 1993 ዓ.ም. ተባርኮ ተከፈተ። በዚሁ ጊዜ ቤተ ክርስቲያኗ አንድ አገልጋይ ካህን ነበራት - አባ ኅሩይ። በአሁኑ ጊዜ አንድ ዲያቆን፤ ሦስት ቀሳውስት፤ አንድ ቆሞስና አንድ ሊቀ ጳጳስ ቤተ ክርስቲያኒቷን በማገልገል ላይ ይገኛሉ። እነኝህ አገልጋይ አባቶች የካህናት ጉባኤን አቋቁመው ሰለ አገልግሎት ተሰባስበው ይመካከራሉ ይወያያሉ። በብጹዕ አባታችን አቡነ መልከጼዴቅ እና በአባቶች ብርቱ ጥረት ከዚህ በፊት ቤተ ክርስቲያኗ ሦስት ዲያቆናትን በማስተማር የድቁናን ስልጣነ ክህነት እንዲቀበሉና እንዲሁም ቤተ ክርስቲያናችንን ለረጅም ጊዜ በዲቁና ማዓረግ ሲያገለግል የነበረው እና አሁን በአስተዳዳሪነት እያገለገለ የሚገኘው ቄስ ወንድምነህ በዚሁ ቤተ ክርስቲያን የቅስና መዓረግ ለመቀበል በቅቷል።
|